EBS TV
VerifiedMedia Company
EBS is a privately held media company established in 2008 in Silver Spring, Maryland, USA to provide a niche transmission programming that targets the booming Ethiopian market globally. Source
Actions
Media Outlet details
| Scope | National |
|---|---|
| Language | Amharic, English |
| Country | United States of America |
|
Similarweb UVM |
Request pricing |
|
Comscore UVM |
Request pricing |
Recent Articles
Search Articles- EBS TV
ለአጠቃላይ ቀዶ ጥገና፣ ለፕላስቲክ ቀዶ ጥገና እና ከአፍ ጤና ሕክምና ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶችን የሚያመርተው የቻይናው ሺጃንግ ወዱ ሜዲካል ኩባንያ ወደ ቂሊንቶ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሊገባ በሚችልበት አግባብ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። የኩባንያውን ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር በዚሁ ጉዳይ የመከሩ ሲሆን ሺጃንግ ወዱ ሜዲካል ኩባንያ በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት ከወሰነ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ይደረግለታል ነው የተባለው፡፡ ኩባንያው በአውሮፓውያኑ 1975 የተመሠረተውና በቻይና ካሉ ትልልቅ የግል ተቋማት አንዱ የሆነው ሄንግዲያን ግሩፕ አካል ሲሆን ግሩፑ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች፣ የፋርማሲና ጤና መጠበቂያ ምርቶች በማምረት የሚታወቅ ነው።
- EBS TV
በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በቴሌ ብር መተግበሪያ የ4 ነጥብ 19 ትሪሊየን ብር የዲጅታል ግብይት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ። ኢንቨስትመንት ሆልዲንግሱ ይሄንን ያለው በስሩ የሚገኙ ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም ግምገማ ለ3ኛ ቀን መቀጠሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው። የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ60 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ያነሳው ተቋሙ ቴሌ ብር በ2018 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 83
You are being redirected...
በኢትዮጵያ 210 ሺህ አርሶ አደሮችን የአየር ንብረት ለውጥ የመድህን ሽፋን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ4 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ። ፕሮጀክቱ ይፋ የተደረገው በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና በአለም የምግብ ፕሮግራም መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ 210 ሺ አርሶ አደሮች በአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች የሚደርስባቸውን ጉዳት እንዲቋቋሙ የሚደግፍ እንደሆነ የአለም የምግብ ፕሮግራም ገልጿል። የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል
- EBS TV
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትላንትናው ዕለት ባካሄደው የ125 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሁለት ባንኮች ብቻ ማሸነፋቸው ተገለጸ፡፡ በውጭ ምንዛሪ ጨረታው 5 ባንኮች ብቻ መሳተፋቸውን የገለጸው ብሄራዊ ባንክ በጨረታው በተሳተፉ ባንኮች የታየው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት 170 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንም ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡ በጨረታው አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ160 ብር ከ20 ሳንቲም የተሸጠ ሲሆን ይህ የጨረታ ውጤት ባንኩ በቅርቡ አካሂዶት በነበረው ጨረታ ከተመዘገበው ውጤት ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ ባንኩ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው የ500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ160 ብር ከ21 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል። በዚሁ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 22 ባንኮች ተሳትፈው ሃያ አንዱ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ከ710 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት አሳይተው ነበር፡፡
- EBS TV
በዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል አንድ እናት ሶስት መንታዎችን በሰላም እንደተገላገሉ የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ወይዘሮ አሲያ ሁሴን የተባሉ እናት በትናንትናው እለት ሶስት መንታዎችን በአፋር ክልል የዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል በሰላም ተገላግለዋል። በአሁኑ ሰዓት የእናትየውም ሆነ የሶስቱ አዲስ ጨቅላ ህፃናት ጤንነት ሙሉ በሙሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሆስፒታሉ ገልጿል። ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ሶስት መንታዎች በአንድ ላይ
- EBS TV
አሜሪካ የህዋ ምርምር ተቋሟ ናሳን ጨምሮ በርካታ የፌደራል ተቋማቷ በቻይና እንደተሰለሉባት ከሰሰች። አሜሪካ እንደምትለው በቻይና መንግስት የሚደገፉት የመረጃ መረብ ሰባሪዎች ናቸው በናሳና በብሔራዊ ባንኳ እንዲሁም በሌሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማት ላይ የመረጃ ምዝበራ ያካሄዱት። ይሁንና የአሜሪካ ባለስልጣናት ምን ያህል ከባድ ሚስጥሮች እንደተዘረፉ የገለፁት ነገር የለም። አሜሪካ ይሄን ክስ ያቀረበችውም ፕሬዝዳንት ትራምፕና የቻይናው አቻቸው ከሳምንት በኋላ በዋሽንግተን ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነው። ይሁንና ቻይና ክሱን ነጭ ውሸት ስትል ውድቅ አድርጋዋለች። በዋሽንግተን የቻይና ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ቤጂንግ ማንኛውንም የሳይበር ጥቃት ታወግዛለች ብሏል።
- EBS TV
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡክ እና መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የ24 ሃገራት ኤምባሲዎች በኢትዮጵያ ሁሉም ወገኖች የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ገንቢ በሆነ መንገድ ለመተግበር ግንኙነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ኤምባሲዎቹ ይሄን ያሉት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጡት አጭር የጋራ መግለጫቸው ነው፡፡ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በወቅታዊ ጉዳዮች ለመመምከር በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ያደረጉትን ጉብኝት እንደሚደግፉት ነው ሃገራቱ በጋራ መግለጫቸው ያስታወቁት። ኤምባሲዎቹ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነ ገልፀዋል።መረጃው ከኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡክ የተገኘ ነው።
You are being redirected...
የሲቪል ማህበራት ቀጣዩ እና የበለጠው ወሳኝ ተግባር የሃገራዊ ምክክሩ ምክረ ሃሳቦችን ወደ ተጨባጭ እርምጃ መቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት አስታወቀ። ም/ቤት ይሄን ያለው የሃገራዊ ምክክሩ መጠናቀቅን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው። ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሃገራዊ ምክክሩ ወቅት በአመካካሪነት ፣በተሳታፊነት ፣ በአማካሪነት እና በታዛቢነት ሚናዎች ላይ በመሳተፍ ገንቢ ሚና መጫወታቸውን ም/ቤቱ አስታውሷል። ም/ቤቱ ሃገራዊ ምክክሩ
- EBS TV
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 15 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱ ተነገረ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ይሄን ያለው በስሩ የሚገኙ ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም ግምገማ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2018 በጀት አመት ያስገባው ገቢ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ60 በመቶ ጭማሬ እንዳለው ነው የተገለጸው፡፡ ባንኩ ለተለያዩ የሃገር ውስጥ
- EBS TV
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አድማስ በማስፋት በኢራን የንግድ አጋር ሀገራት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ ቻይና ጥቅሞቿን ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ እንደምትወስድ አሳሰበች፡፡ የቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ዋሽንግተን በቴህራን ላይ የጣለችው የተናጥል ማዕቀብ ህገ ወጥ ነው ሲሉ ያወገዙ ሲሆን ቤጂንግ መብቶቿን ለማስከበር መውሰድ ያለባትን እርምጃ ሁሉ ትወስዳለች ብለዋል፡፡ ቻይና ይህን ማሳሰቢያ ያወጣችው ደግሞ የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት ከኢራን ጋር የሚነግድ ማንኛውም ሀገር ላይ የማግለል እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ካስጠነቀቁ በኋላ ነው፡፡ አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ መጠኑ ቢቀንስም ቤጂንግ የኢራንን ነዳጅ በገፍ ከሚገዙ የዓለማችን ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ እንደሆነች ይነገራል፡፡ በቻይና እና ኢራን...